Wednesday, December 10, 2014

የኢህአዴግ አመራሮች በሚፈጥሩት ተንኮል በትግራይና አማራ ተወላጆች መካከል አሁንም ግጭቶች እየቀጠሉ በመሆናቸው ምክንያት የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት ቀደም ሲል ሲደረግ የነበረውን በትግራይና በአማራ ተወላጆች መካከል የማጋጨት ተግባር አሁንም አጠናክረው በመቀጠል ህዳር 20/2007 ዓ/ም በሰሜን ጎንደር፤ ታች አርማጭሆ ወረዳ፤ ልዩ ስሙ አዋጠር በተባለው ቦታ የማይፀብሪ ተወላጅ የሆነውን ኤፍሬም መብራህቱ ለተባለው  ሾፌር እህል ጭኖ ይጓዝ በነበረበት ሰዓት ለግዜው ስሙ ባልታወቀው በአካባቢው ነዋሪ መገደሉንና ጭኖት የነበረው እህልም መቃጠሉ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ የኢህአዴግ መሪዎች ህዝቡ ተባብሮ በላያቸው ላይ የተቃውሞ አድማ እንዳያደርግባቸው ስጋት ስላደረባቸው ከፋፍለህ ግዛ የሚል ፖሊሲያቸውን በመጠቀም በስውር ህዝቡ እርስ በራሱ እንዲናቆር እያደረጉ መሆናቸውንና በዚህም ምክንያት በብሄሮች መካከል ከባድ የደም መፋሰስና የህይወት መጥፋት  እያጋጠመ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።