በትግራይ ክልል በተምቤን ዓብይ-ዓዲና ሃገረሰላም
አካባቢ የሚኖረው ህዝብ። ስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ማግኘት የሚገባውን ፖለቲካዊ ነፃነትና ማህበራዊ አገልግሎት አስመልክቶ በተለያዩ
አጋጣሚዎች ቢጠይቅም በህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች እየተሰጠው ያለው ምላሽ ግን ዛቻ፤ ማስፈራራትና፤ በተጨማሪም ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ
ብለው ላስቀመጧቸው ንፅኃን ሰዎችም በስውር እያሰሯቸውና ደብዛቸውን እያጠፏቸው እንደሆኑ የተገነዘበው ህዝብ ደርግን አጥፍተን ሌላ
ስሙን የቀየረ ደርግ አመጣን በማለት በስርዓቱ ላይ ያለውን ጥላቻ እየገለፀ መሆኑን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
በአሁኑ ግዜ በትግራይ ክልል የሚኖረው ህዝብ ከማንኛውም በላይ ሰብአዊና
ዴሞክራሲያዊ መብቱ መረገጡን የገለፀው መረጃው የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣኖች እያካሄዱት ባለው ስብሰባ ህዝቡ በስርአቱ ላይ ያሚያነሳውን
ጥያቄና አስተያየት ሰምተው ለማፈንና ለማሰር እየተጠቀሙበት ያለው የአምባ-ገነኖች ስብሰባ ነው በማለት ህዝቡ እየተነጋገረበት እንደሆነ
ለማወቅ ተችሏል።