Sunday, December 14, 2014

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖረው ህዝብ እያንዳንዱ እንቅስቃሴው በኢህአዴግ የደህንነት አባላት ጥብቅ ክትትል እየተደረገበት በመሆኑ እለታዊ ስራዎቹን ማሳለጥ እንዳልቻለ ተገለፀ።



በምጮቻችን መረጃ መሰረት ሰላማዊ ትግል የሚያካሂዱ ተቃዋሚ ድርጅቶች ከነዋሪው ህዝብ ጋር በመሆን ስርአቱን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጠይቀው ስላልተፈቀደላቸው በተሰጠው አፋኝ መልስ ግርግር ያነሳሉ የሚል ስጋት ያደረባቸው የኢህአዴግ ባለስልጣኖች በርካታ የደህንነት አባላት በማሰማራት የእያንዳንዱን ሰው እንቅስቃሴ፤ ማን ከማን ጋር እንደተገናኘና ምን አይነት ስራ እየሰራ እንደዋለ በጥብቅ እየተከታተሉት መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
     መላው የከተማው ማህበረሰብ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ክትትል እርስ በራሱ ተረዳድቶና ተባብሮ ሰርቶ እለታዊ ኑሮውን እንዳይመራ እጅግ ተቸግሮ እንደሚገኝ የገለጸው መረጃው የኢህአዴግ መሪዎች ሊካሄድ በታሰበው ምርጫ ላይ ምን ያህል ስጋት ላይ እንደወደቁና ከህዝቡ ተነጥለው እንደሚገኙ የሚያረጋግጥ እንደሆነ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።