Friday, December 19, 2014

በዓዲ ጎሹና አካባቢው ከገበሬዎች የተወረሰውን ሰሊጥና ማሽላ አስተዳዳሪዎችና የፖሊስ አዛዦች እየሸጡት እንደሚገኙ ተገለፀ።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት ህዳር 25/2007 ዓ,ም በዓዲ ጎሹና አካባቢው የተከለከለ መሬት አርሳችኋል በሚል ምክንያት ከድሃ ወገኖቻችን የተወረሰ በርካታ ሰሊጥና ማሽላ በአካባቢው የሚገኙ የቀበሌ አስተዳዳሪዎችና የፖሊስ አዛዦች ተመሳጥረው ሽጠው እየበሉት መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
  እነዚህ ያልደከሙበትን በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ ከሚገኙት የስርዓቱ ወሮበላ ካድሬዎች ውስጥ አለማየሁ ታፈረ የተባለ ፖሊስ፤ የፀጥታ ሃላፊው ካሳሁን አለበልና የቀበሌው ሊቀመንበር የሚገኙባቸው ሲሆኑ አግባብነት በሌለው መንገድ የተወረሰው እህላችን አስተዳዳሪዎችና ፖሊሶች ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት ነው በማለት ከከሰሱ ገበሬዎች ውስጥ ደግሞ ጉዕሽ መኮነን ከሰለኽለኻ አካባቢ የመጣና ወልደዳዊት ተጠምቀና ተኪኤ ጉዕሽ የተባሉ የሚገኙባቸው ሲሆኑ እስካሁን ግን ምንም አይነት መፍትሄ ማግኘት እንዳልቻሉ የደረሰን መረጃ አክሎ አስታውቋል።