Friday, December 19, 2014

በዓዲ ነብሪኢድ አካባቢ ለመንገድ መስርያ ተብሎ የተዘጋጀ ንብረት የኢህአዴግ ብዱን የሰራዊት አባላት እየሰረቁ በመሽጥ ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።



    ምንጮቻችን ከቦታው የላኩልን መረጃ እንደሚያመልክተው በዓዲ ነብሪኢድ ማይ ዓሶ በተባለ ልዩ አካባቢ ለመንገድ መስርያ ተብሎ በቻይናውያን የቆመ ፕሮጀክት ሰራተኞቹ ወደ ሌላ ቦታ በሄዱበት ሰዓት በፕሮጀክቱ የቀረውን ንብረት ህዳር 24/2007 ዓ.ም የገዥው ኢህአዴግ ስርዓት የሰራዊት አባላት እንደሸጡት ለማወቅ ተችሏል።
በስርቆት ስራ ላይ የተሰማሩ የሰራዊት አባላት የ22ተኛ ክፍለ ጦር አባላት ሲሆኑ እንዲጠብቁት የተሰጣቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ወደ ሽሬና ሽራሮ ከተሞች ጠብቁት የተባሉትን እንደ ማሽን፤ የመኪና ጎማዎችና ሌሎችንም ንብረቶች እየሸጡት እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ይህንን ተግባር እየፈፀሙ ከሚገኙት የሰራዊቱ አባላትም አምሳ አለቃ ብርሃነ ሓረጎትና አስር አለቃ ከዋኒ የተባሉ ሲሆኑ ይህንን አስነዋሪ ተግባር እየፈፀሙ ያሉትም በከፍተኛ አመራሮች ታዘው ሳይሆን እንደማይቀር የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
    በተመሳሳይ የማዕከላዊ እዝ 8ተኛ ክፍለ ለጦር መካናይዝድ አዛዥ በርጋዴል ጀኔራል መሓመድ ብርሃን(ወዲ ጎጀላ) ለስራ እንዲያሳልጥበት ተብሎ የተረከበውን አንድ ቦጥ መኪና ሙሉ ነዳጅ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ በሚገኝ ጉዕሽ ክፍላይ በተባለ የነዳጅ ማደያ ሲሸጥ እንደተገኘ ከዚህ በፊት በዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወቃል።