በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ
የሚገኙ የተለያዩ 11 ባንኮች ከጥር 4/2007 ዓ.ም ጀምረው የተለመደ ስራቸውን ማሳለጥ ስላልቻሉ በባንኮቹ የሚጠቀመው ማህበረሰብ
ምሬቱን እያሰማ እንደምሚገኝ የገለጸው ይህ መረጃ የዚህ መነሻ ምክንያትም ስርዓቱ በአካባቢው ፈጥሮት ባለው ያለመረጋጋት የተነሳ ቀጣይነት ባለው ስብሰባ ውስጥ
ተጠምዶ ስለሚገኝ ኔት-ዎርክ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውና እነዚህ ባንኮች ደግሞ ዕለታዊ ስራዎቻቸው ከኔት-ዎርክ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ሁሉም ባንኮች በአሁኑ
ሰዓት ስራዎቻቸውን አቁመው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ በፊት ባሰራጨነው የዜና እወጃችን በምዕራባዊ ዞንና አካባቢው የስልክ
አገልግሎት ተዘግቶ ስለሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴውን በተገቢው መንገድ እንዳይመራ ተቸግሮ እንደሚገኝ
ገልፀን እንደነብርን ይታወሳል።