Wednesday, January 28, 2015

የህወሃት ካድሬዎች ለትግራይ ክልል ህዝብ በአስገዳጅ እያደሉት ያለው የመርጫ ካርድ ህዝቡ ለማን ነው የምንመርጠው እያለ የተሰጠውን ካርድ እየመለሰላቸው እንደሚገኝ ተገለፀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች ህብረተሰቡን የምርጫ ካርድ ወሰድ እያሉ ከቤቱ በአስገዳጅ እያሰወጡ የምርጫ ካርድ ወደሚታደልበት ቦታ ቢወስዱትም ህዝቡ ግን አንመርጥም በማለት የተሰጠውን የምርጫ ካርድ ጥሎላቸው እየተመለሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው አክሎ ካርድ አንወስድም በማለት እየተመለሰ ባለው ህዝብ የተናደዱት የህወሃት ካድሬዎችና አስተዳዳሪዎች ምን ሁናችሁ ነው የምርጫ ካርድ የማትወስዱ ብለው በሚጠይቋቸው ሰዓት የሚወዳደር የፖለቲካ ፓርቲ በሌለበት ሃገር ማንን ልንመርጥ ነው ካርድ የምንወስደው ኢህአዴግ ብቻውን አይደለም እንዴ ለመወዳድር ላይና ታች እያለ የሚገኘው በማለት ሃሳቡን እንደተቃወሙት መረጃው አስረድቷል።