በምንጮች
መረጃ መሰረት በጎንደር ከተማ እንዲሁም በመተማና በሳንጃ ወረዳዎች የሚገኘው ህዝብ ጥር 6 /2007 ዓ/ም የምርጫ ካርድ አንወስድምና አንመርጥም በማለት ታቅቦ እንደሚገኝ በተለይ የሳንጃ ወረዳ
ህዝብ መሬት የሚዘርፍ መንግስት አንፈልግም! አንመርጥም! ማለታቸውን አስረድቷል።
መረጃው ጨምሮ
እንደገለፀው የሳንጃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን እንደሻው የተባሉት የስርአቱ ባለስልጣን ከህዝብ ጋር ወግነህ ውስጥ ለውስጥ
መንግስትን ትቃወማለህ በሚል ምክንያት ከነ አቶ ይስፋው አለበልና ጌትነት ምእራፍ ጋር በስርዓቱ ታስሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።