በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በሽሬ፤ ሽራሮና አስገደ-ፅምብላ የሚገኙ የስርዓቱ
ካድሬዎች ጥር 5/ 2007 ዓ/ም የምርጫ ካርድ ያልያዘ ሰው የህክምናና የፍትህ አገልግሎት እንደማያገኝና እንዲሁም እንደ ስኳርና
ዘይት የመሳሰሉ አቅርቦቶችንና ሌሎችንም አጠቃላይ ማህበራዊ አገልግሎቶች አታገኙም በማለት እየከለከሏቸው መሆኑ ተገለፀ።
በየኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የይስሙላ ምርጫ ተስፋ ያጣው የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ
ዞን ኗሪ ህዝብ አብዛኛው የምርጫ ካርድ እንዳልወሰደ የገለፀው መረጃው ወደ ህክምናና ፍርድ ቤቶች በሚሄድበት ጊዜም መጀመሪያ የሚጠየቀው
የምርጫ ካርድ መያዙን ሲሆን ያልያዘ ሰው ደግሞ አገልግሎት አታገኝም እየተባለ እንደሚባረር አስረድቷል።
ይህ እኩይ
አሰራር ገዥው መንግስት የዕድሜ ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ህዝብ ያላመነበትን የምርጫ ካርድ ለሽማግሌዎች በአስገዳጅ እድሜ በታች ለሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ደግሞ በአንድ ለአምስት የተጠናከረ የቤተሰብ ውስጥ የስለላ
መዋቅር በወላጆቻቸው አማካኝነት እየተፈጸመ መሆኑን በመላው የሃገራችን አካባቢ መነገገሪያ አጀንዳ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።