ምንጮቻችን እንደገለፁት በደቡብ ክልል፤ ከንባታ
ዞን፤ ዱራሜ ከተማ ውስጥ የሚኖረው ህዝብ በመጪው ግንቦት ወር 2007 ዓ/ም ለሚካሄደው አስመሳይ ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ የሚያገለግል
ካርድ እንዲወስድ በስርዓቱ ካድሬዎች የቀረበለትን ጥሪ እንዳልተቀበለው የገለፀው መረጃው በህዝቡ ተቃውሞ የተደናገጡ የወረዳው እስተዳዳሪዎችም
በአስገዳጅ ስብሰባ ላይ ጠምደውት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ የዱራሜ ከተማ ህዝብ በኢህአዴግ ስርዓት ላይ እምነት በማጣቱ
2002 ዓ/ም በሟሟያ ምርጫ ላይ አንመርጥም ብሎ ተቃውሞ ማሰማቱ የታወቃል።