እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል፤
ምስራቃዊ ዞን፤ አፅቢ ወንበርታ ወረዳ፤ ሓየሎም ቀበሌ ልዩ ስሙ ቀጸሎ በተባለው አካባቢ በገዢው ብዱን ባለስልጣኖች ለነዋሪው ህብረተሰብ
ሳያሳውቁ ጥር 6 /2007 ዓ/ም የጀመሩት የምልሻ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት እስከ አሁን ድረስ አቶ ሕሸ ገብሩ የተባለው አርሶ አደር የሚገኙባቸው ሰዎችና በርከት ያሉ
እንስሶች እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
እንዲህ ያለ ሃላፊነት የጎደለው የምልሻ ማሰልጠን ተግባር። በሁሉም የትግራይ
ዞኖች እየተካሄደ እንዳለና በሰው፤ በእንስሳትና በንብረት ላይም ከፈተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ከኣካባቢው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።