ምንጮቻችን ከአካባቢው እንደገለፁት በሰሜን
ጎንደር ዞን፤ በሳንጃ ወረዳ የሚኖረው ህዝብ ጥር 7/2007 ዓ/ም
መነሻውን የመሬት ጥያቄ ያደረገ አድማ ተከትሎ ለወረዳው አስተዳዳሪ ያንተ እጅ አለበት በማለት ሌሎችን ሦስት ሰዎች ጨምሮ በእለቱ 12 ሰዓት ምሽት
ላይ የብአዴን ኢህአዴግ ባለ ስልጣኖች አፍነው በመውሰድ እንዳሰሯቸውና ከግንቦት 7’ና ከሌሎች ድርጅቶች ጋርም ስትገናኙ ቆይታችኋል
በማለት በላያቸው ላይ ከባድ ምርመራ እያካሄዱባቸው መሆናቸውን መረጃው አስታውቋል።
በዚሁ ሁኔታ ከታሰሩት መካከል- የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን
እንደሻው፤ ይስፋው አለበልና ጌትነት ምእራፍ የተባሉ ሲሆኑ ይህ እየተወሰደ ያለው የማሰር እርምጃ ዋናው ምክንያትም የትጥቅ ትግል
የሚያካሂዱ ድርጅቶች በአካባቢው ላይ ትልቅ ተቀባይነት በማግኘታቸው የተነሳ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ስርዓት አገልጋዮቹ የነበሩትን
ባለስልጣኖችም ጭምር በማሰር ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል።