Friday, January 30, 2015

የሰለኽለኻ ከተማ ነዋሪ ህዝብ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ በስርአቱ ካድሬዎች የተደረገላቸውን ጥሪ በመቃወም የምንወስደው ካርድና የምንመርጠው ሰው የለንም በማለት የተቃውሞ መልስ እንደሰጡ ተገለፀ።



በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን የሰለኽለኻ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በመጪው ግንቦት ወር 2007 ዓ/ም ለሚካሄደው አስመሳይ ምርጫ የሚሆን የምርጫ ካርድ እንዲወስድ በህወሃት ኢህአዴግ ቡድን የቀረበላቸውን ጥሪ አንወስድም፤ የምንመርጠው አካልም የለንም ብለው መቃወማቸውን የገለፀው መረጃው ካርዱን እንዳይወስዱ ያነሳሳቸውን ምክንያት ሲገልፁም ገዢው ስርዓት እንደዜጎቹ አያየንም፤ መኖርያ ቤታችንን በዶዞር አፍርሶ ሲያበቃ ተለዋጭ መሬትና ካሳ ሳይሰጥ በአውላላ መሬት ላይ የጣለንና ፍትህ ጠቅልሎ እንዲጠፋ ላደረገ ስርዓት አንመርጥም ማለታቸውን የተገኘው መረጃ አስታውቋል።
   መረጃው በማስከተል ከ65 ሺህ በላይ የሰለኽለኻ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ስርዓቱ ህጋዊ ቤታቸውን ጥር 9/ 2007 ዓ/ም ዶዞሮችን በማሰማራት ማፍረሱንና ህዝቡ ለምን እንደፈረሰ ለሚመለከታቸው አካላት ቢጠይቅም ተገቢ መልስ ሳይሰጣቸው እስካሁን ድረስ በረሃ ላይ ተጥለው እንደሚገኙ የገለጸው መረጃው በስርዓቱ ስር ሆነን የምንመርጥበት ሁኔታ የለም በማለትም ተመዝገቡና ካርድ ውሰዱ የሚለውን ጥሪ እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል።
   አስመሳይ የህወሃት ኢህአዴግ ምርጫን አስመልክተው በግልፅ ከተቃወሙት ግለሰቦች መካካል ወ/ሮ ግደይ አበበ፤ አቶ ፀጋይ ገብረመስቀልና አቶ ዘነበ ፍትሃነገስ የሚገኙባቸው በርካታ የከተማው ነዋሪዎች እንደሆኑ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።