የኢህአደግን ስርአት መጥፎ አሰራር በመቃወም ከተባረሩት የመከላከያ ሰራዊት
ከፍተኛ መኮንኖች አንዱ ሌተናል ጀነራል አበባው ታደሰ ንብረቱ በስርአቱ ካድሬዎች እየተቀማ እንዳለ የገለፀው ይህ መረጃ በመሆኑም
በባህር ዳር ከተማ ያሰራውን መኖሪያ ቤት ሸኽ አላህሙዲን በ300 ሚልዮን ብር ከገዛው በኋላ በገንዘቡ ርክክብ ጊዜ ተከታትለው ገንዝቡ
እንዲያዝ እንዳደረጉት ታውቋል።
አበባው ታደሰ የሸጠው መኖሪያ ቤት በመከላከያ ሰራዊት እያለ ያሰራው መሆኑ
የገለፀው መረጃው ይሁን እንጂ ከስርዓቱ ጋር እያለ ያልተቀማ አሁን ከስራው ከተባረረ በኋላ በስርአቱ እየተወሰደ ያለ እርምጃ ቅንነት
የጎደለው አካሄድ በመሆኑ እነዚህ ያልተባረሩ የሰራዊቱ አባላት ያሰሯቸው
ቤቶች ለምን አያስረከቡም በሚል በሰራዊቱ ውስጥ ይሁን በህዝቡ ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ
ሁኖ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።