ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ እንደሚያመላክተው ከጥር 25 /2007 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የየካቲት ዘመቻ በሚል ለተከታታይ 20 ቀናት ሁሉም ሰው የነፃ አገልግሎት ለመስጠት ወደ ግድቡ ስራ እንዲዘምት በህወሃት ካድሬዎች መመሪያ መውረዱና በተለይ ደግሞ በናዕዴር አዴት ወረዳ በሰፊው እየተሰራበት እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
የትግራይ ህዝብ ግን የካቲት 11 የምንወዳቸውን ልጆቻችንንና ወንድም እህቶቻችንን በህይወት ገብረን ያገኘነው አንዳች ነነገር የለም ስለዚህ አሁን እየተደረገ ያለውም ጉልበታችንን ለመበዝበዝና ለፖለቲካዊ መነገጃ
ካልሆነ በስተቀር ከየካቲት ወር የምንጠብቀው አዲስ ነገር ስለሌለ በነፃ የምንሰራው ነገር የለንም በማለት እንደተናገሩ የገለፀው ይህ መረጃ በተለይ ደግሞ ከእጅ ወደ አፍ እየሰሩ የሚተዳደሩ ወገኖቻችን የጉልበታችን ዋጋ ይከፈለን በነፃ ስራ ላይ እየዋልን ምን እንበላለን በማለት መመርያውን እንደተቃወሙት መረጃው ገልጿል።
በህዝቡ
ተቃውሞ የተደናገጡት የህወሃት ከዳተኛ ካድሬዎች በየካቲት ዘመቻ ያልዘመተ የሰማታትን አጥንት እንደረገጠ ይታሰባል ቢሏቸውም ህብረተሰቡ ግን የሰማታትን አጥንት ረግጣችሁ ለግል ጥቅም እየተሯሯጣችሁ ያላችሁስ እናንተው እራሳችሁ ናችሁ እኛስ የሰማታት አደራ ሁልጊዜ በልባችን ውስጥ አለ በማለት እንደመለሱላቸው የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።