Wednesday, February 11, 2015

በሁመራ ከተማ የሚገኙ አርሶ-አደር የተቀማ መሬታችን ይመለስልን ብለው በሚጠይቁበት ግዜ መፍትሄ የሚሰጥ የምንግስት አካል በማጣታቸው ምክንያት ምሬታቸውን በማሰማት ላይ እንዳሉ ታወቀ።



መሬታቸው የተቀሙት አርሶ አደሮች ባለሃብቶች ምፍትሄ እንዲደረገላቸው ሰሰን የተባለ የወረዳው የመሬት አስተዳደር ጥር 18 2007ዓ/ም የቀረበለትን አቤቱታ አንመልስም ከፈለጋችሁ ለዞን አስተዳደር ጠይቁ ስለተባሉ ወደ ዞን አስተዳደር በሄዱበት ግዜ ደግሞ ተመሳሳይ ምላሽ እንደተሰጣቸው ያገኘነው መረጃ አስረድቷል።
መረጃው በማከል በተለያዩ ችግሮች ተማርሮ መፍትሄ ለማግኘት አቤቱታው የሚያሰማ ወገን የሚያየው አካል አጥቶ ስራውን በመተው  ከቢሮ ወደ ቢሮ ሲንከራተት እየዋለ እነዳለ ከገለፀ በኋላ የፈለጉትን የጉቦ መጠን የከፈለ ሰው ግን አቤቱታውን እንደሚሰሙለት መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።