Wednesday, February 11, 2015

የኢህአደግ ጉጅሌ በደደቢት ላይ ከነበሩት የመስኖ ስራ ባለሃብቶች ለስዃር ፋብሪካ እንዲውል በማለት ቀምቶ የወሰደው መሬት ለሌሎች እንደሰጠው ተገለፀ።



በደደቢትና አካባቢው ከሚገኙ የመስኖ ስራ ባለሃብቶች አካባቢው የህወሓት ካድሬዎች መንግስት ለስዃር ፋብሪካ ሰለሚፈልገው በአመት 500 ብር ካሳ ይከፍላችኋል ልቀቁ በሚል ተለዋጭ መሬት ሳይሰጡ እንዳባረሯቸው የገለፀው መረጃው እነዚህ መሬታቸው የተቀሙ ወገኖች ኑሯችንን ልንመራበት ካሳ ይሁን ተለዋጭ መሬት ይሰጠን በማለት ጥር 16/ 2007ዓ/ም ወደ የሰሜን ምእራብ ዞን የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ ወደ ኢሳያስ ታደሰ ባቀርቡበት ግዜ የማውቀው ነገር የለኝም መሬቱንም አድለነዋል ሲል እንደመለሰላቸው ታውቋል።
  መሬታቸው በስርአቱ ተቀምተው ብሶታቸውን በማቅረብ ላይ ካሉት መካከል አብረሃለይ ተኽለ፤ እንዲሁም ስሙ በውል ያልታወቀው በወዲ ራያ የሚታወቅና ሌሎች የሚገኙበት ሲሆን ቀድሞውንም ለስዃር ፋብሪካ ምክንያት ብላችሁ ጉቦ ለሚሰጣችሁ ሰው ለማደል የተጠቀማችሁበት መላ ነው እንዳሉዋቸው ለማወቅ ተችሏል።