Saturday, March 21, 2015

በማእከላዊ እዝ ውስጥ የሚገኙ የኢህአዴግ 31ኛ ክፍለ ጦር አባላት በብዛት እየከዱ በመሆናቸው ምክንያት የተነሳ። ከፍተኛ አዛዦቻቸው በሃይለኛ ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ታወቀ፣



ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ባገኘነው መረጃ መሰረት። በማእከላዊ እዝ ውስጥ የሚገኙ የ31ክፍለ ጦር 3ና 7 ሬጅመንት የሆኑት የሰራዊት አባላት። በአንድ ወር ብቻ በርከት ያሉ አባላቶቹ በመክዳታቸው የተነሳ። ከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች ስጋት ላይ መውደቃቸው ለማወቅ ትችሏል፣
    በዚህ የተነሳም። ከክፍለ ጦሩ ውስጥ የ3ና 7ሬጅመት አባላት በብዛት በመክዳታቸው ምክንያት። ከየካቲት 23 /2007 ዓ/ም ጀምረው ከሬጅመት እስከ ሃይል ያሉት አዛዦች። በሃይለኛ ግምገማ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል፣