በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በአማራ ክልል ጎንደር አካባቢ ልዩ
ስሙ ወረታ በተባለው ስፍራ። በደመቀ መኮነን የተመራ ስብሰባ እንደተካሄደ የገለፀው መረጃው። እናንተ እንደ ስእል በወንበር ላይ
ቁጭ አላችሁ እንጂ የሰራችሁት ስራና ያማጣችሁት ለውጥ የለም በማለት። በመድረኩ መሪ የተደረገላቸውን ቅስቀሳ በህዝቡ ተቀባይነት
ሳያገኝ ስብሰባውም ሳይረዳዱ እንደተበተነ ታወቀ፣
የምርጫ ወቅት በተቃረበበት ጊዜ። የኢህአዴግ መሪዎች አይተዉት የማያውቁትን
ህዝብ ወደየ ቀበሌያቸው በመዞርና ስብሰባ በመጥራት ስራውን ትቶ ስብሰባ ላይ እንዲውል እያደረጉት መሆናቸውና። ህዝቡ በበኩሉም የት
ታውቁናላችሁ አሁን ምርጫ ስለተቃረበ በስብሰባ አታስጨንቁን እያላቸው መሆኑን። ምንጮቻችን ጨምረው አስረድተዋል፣