በመረጃው መሰረት። በአማራ ክልል የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች በወያኔ
ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት አስተዳደር የሚወርድባቸውን ግፍ ለመግታትና ለመግለፅ የተለያዩ ተቃውሞዎችን በማካሄድ ብሶታቸውን እየገለፁ
የሚገኙ ሲሆን። የከተማዋ ባለስልጣናትም ሊፈጠር የሚችለውን ህዝባዊ ማዕበል በመስጋትና በመጪው ምርጫ ላይ እንቅፋት እንዳይፈጠርባቸው
በማለት። ይህንን ተቃውሞ ለማቆምና የከተማዋን ነዋሪ ህዝብ ለመደለል ለመኖሪያ ቤት መስሪያ መሬት እያደሉ ቢሆኑም። ህዝቡ ግን በዚህ
ሊደለል እንደማይችል ሊታወቅ ተችሏል፣
በተመሳሳይ
ከባህር ዳር ከተማ ሳንወጣ የስርዓቱ ካድሬዎች በከተማው ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ሲሉ ከ86 በላይ የስልያ
ሰራተኞችን በማሰማራት ህዝቡን እየረበሹ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው። እነዚህ የስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ የሆኑ ተላላኪዎች በየመጠጥ
ቤቱና በየትምህርት ቤቶች እንዲሁም በቤተክርስትያንና በመስጊዶች በመሰማራት። ህብረተሰቡን በማስፈራራት ስራ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ።
ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለክቷል፣