Sunday, April 12, 2015

በአማራ ክልል የሚገኘው ህዝብ። ከአሸባሪዎች ጋር ግንኝነት አለህ በሚል ምክንያት። በስርአቱ አስተዳዳሪዎች ማስፈራራትና ዛቻ በተሞላበት ስብሰባ ላይ ተጠምዶ እየዋለ መሆኑን። ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣



     ከተለያዩ የአማራ ክልል የወረዳ መስተዳድሮች ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው። ከመጋቢት 6 እስከ 12/2007 ዓ/ም። ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ ያሉት የህዝቡ የግንኝነት ሃላፊዎች። በዞንና በወረዳ ውስጥ የሚገኘውን ህዝብ በመሰብሰብ። ለፀረ ሰላም ሃይሎች ትተባበራላችሁ በማለት። በተከታታይ ስብሰባ ላይ ጠምደውት እንደሰነበቱ ለማወቅ ተችሏል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ። በስብሰባው ላይ የተገኘው ህዝብ። እንደናንተ ያለ የህዝብ ኃላፊነት የማይሰማው ድርጅት አይመራንም፤ ለውጥ የሚያመጣ ድርጅት ካገኘን ዛሬ ይሁን ነገ መደገፍ እንችላለን፤ ከፀረ ሰላም ሃይሎች ትተባበራላችሁ የምትሉት ግን። ከእውነት የራቀ ነው ብለው መልስ መስጠታቸውንና። በካድሬዎቹና በህዝቡ መሃል ንትርክ በመፈጠሩ ምክንያትም። ስብሰባው ያለ አንዳች ፍሬ መበተኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣