እንደምንጮቻችን ገለፃ በክልሉ በሚገኙ ዞኖች
እየተካሄደ ባለው የ6 ወር አጠቃላይ የግብርና ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ከመጋቢት 21 እስከ 29/ 2007 ዓ/ም ለተከታታይ 8
ቀናት በዞን አመራሮችና በግብርና መምሪያ ሃላፊዎች መድረክ መሪነት።
በሃገሪቱ ገጠራማ ክፍሎች መሰራት የሚገባቸው ወቅታዊ ስራዎች
እቅድና ክንውን ምን ይመስላል? ሟሟላት የሚገባንንስ አሟልተናል ወይ? በሚል አጀንዳ ግምገማው የቀረበ ሲሆን በበርካታዎች ዘንድ
ከባድና ገዥውን መንግስት ለውድቀት የሚያጋልጥ ነባርዊ ሃቀኛ ህዝባዊ ጥያቄዎች መነሳታቸውን አብራርተዋል፣
በየዞኑ ከተነሱት ያልተከናወኑ በርካታ የተለያዩ ጥያቄዎች መካከልም።-
በአመታዊ በጀት ፀድቀው ክፍያ ተፈጽሞባቸው የተገዙ በሺዎች የሚቆጠሩ
የባለሙያ ተሽከርካሪዎች ማለትም ሞተር ሳይክልና ብስክሌት እስከ ቅያር ክፍሎቻቸው ለባለሙያው ለምን አልታደሉም? የባለሙያው
ጥቅማጥቅሞች አለመከበራቸውና የዲግሪና የማሻሻያ ትምህርት በዝምድናና በጥቅም መላክ? የሞቃትና የቀዝቃዛ አካባቢዎች አልባሳት ለባለሙያው አለመሰጠት። በክህሎት ዝቅተኛ
የሆኑና ከትምህርት ሙያቸው የማይገናኙ ግለሰቦች በአመራርነት ቦታ መቀመጥ እንዲሁም ጀግናው ገበሬ የተባለው ትራክተር፤ የወተት መናጫ፤
የማር ማጣሪያና የጀኔሬተር አቅርቦቶች ለማሰልጠኛ ማዕከል አለመቅረባቸው የሚሉት የተነሱ ሲሆን አንዳንድ ባለሙያዎችም ወደፊት በስራቸው
እንደማይቀጥሉ መናገራቸውን ምንጮቻችን ጨምረው አስረድተዋል፣