በመቐለ ከተማ የሚገኙ የገዥው ቡድን ህወሃት
ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. አስተዳዳሪዎች የከተማዋን ነዋሪ ህዝብ በመሰብሰብ መንግስት ምርጫ ለማካሄድ እያደረገ ባለው ዝግጅት ላይ እንቅፋት
የሚሆኑ ሰዎች ወደ ከተማዋ ገብተው ስላሉ ወጣቶች ይሁኑ ከእድሜ በታች የሆኑ ህፃናት ምርጫ እስኪያልፍ ድረስ በጎዳና ላይ እንዳይንቀሳቀሱ
ወላጆቻቸው አስፈላጊውን ክትትልና ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው የሚል ትዕዛዝ እንዳስተላለፉ ታወቀ።
ተሰብሳቢው ህዝብ በበኩሉ ይህ የፀጥታ ስጋት አለ እያላችሁ ለህብረተሰቡ
እያሸከማችሁት ያላችሁት በፀጥታ አባሎቻችሁ የሚደረግ እንጂ ሰላማዊውን ህዝብ የሚመለከት አይደለም እነዚህ ወደ ውጭ እንዳይወጡ እያላችሁን
ያላችኋቸው ወጣቶች ምን እንዲበሉ ነው ቤት የምንዘጋባቸው ሰርታችሁ አትብሉ የሚባል ነገር የለም በማለት ሃሳባቸውን እንደተቃወሙት
ምንጮቻችን ገለፁ።