የጎንደር ከተማ ከንቲባ ህዝቡ በስርዓቱ ላይ ያለው እምነት ማሽቆልቆሉና
በመጪው ምርጫ ላይ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ሊመርጥ ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበት ህዝቡን በማይተገበር ቃል ለመደለል ሲል ለመንግስት
ሰራትኞችና ነጋዴዎች ግንቦት 7/2007 ዓ/ም በመሰብሰብ በማህበር ከተደራጃችሁ ለቤት መስሪያ የሚሆን መሬት እንሰጣችሁአለን ብሎ
ለማደናገር ቢሞክርም ህዝቡ ግን መሬት የመንግስት ስለሆነ በሊዝ ነው የሚሰጠው እያላችሁ እንዳልቆያችሁ አሁን ላይ ደርሳችሁ እናድላችኃለን
ማለታችሁ እንድትመረጡ የደረጋችሁት መላ ነው ብሎ እንደመለሰላቸው
ለማወቅ ተችሏል።
እነኝህ የመንግስት ሰራተኞችና ነጋዴዎች በከንቲባው የቀረበውን የማይተገበር
ቃል በመቃወም ምርጫው ካለፈ በኋላ አታስታውሱንም፤ ካለፈው ተግባራችሁ ተምረናል በማለት ወጣት መኳንንት አለባቸው፤ አዲስ ታፈሰና
ሌሎች የሚገኙባቸው ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ መረጃው አክሎ አስረድቷል።