ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል ከተቀላቀሉ ወጣት
ዜጎቻችን መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል።-
1.
ወጣት ጎዳዳይ ተስፋይ ግርማይ ከአማራ ክልል፤ሰሜን ጎደር ዞን፤ ደባርቅ
ወረዳ አባይ ሰቆር ቀበሌ፤
2.
ዳንኤል ሰለለው ገብረኪዳን ከትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን ሰቲት ሁመራ
ወረዳ 02 ቀበሌ ቀጠና 2፤
3.
ክብሮም አረጋይ ገብረዋህድ ከትግራይ ምእራባዊ ዞን ሰቲት ሁመራ ወረዳ 03 ቀበሌ ቀጠና 5፤
4.
ማሙሽ አሸናፊ ቸኮል ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ቀራቅር ወረዳ ስፍራ
ቀበሌ ቀጠና ሰፍራ ሊቃ፤
5.
ገብርሄት ነጋ ገረንችኤል በትግራይ ምእራባዊ ዞን ዓዲ ረመፅ ወረዳ ሽሬላ
ቀበሌ፤ ዓዲ ጢኖ ቀጠና፤
6.
ክብሮም ካሕሳይ ገብሪሃንስና ባህረ ዓማር ጋሼ ሁለቱም ከትግራይ ምእራባዊ
ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ዓዲ ጎሹ ቀበሌ፤
7.
አታሉ ተስፋ አሰፋ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ቀራቅር ወረዳ ሸኒ
ቀበሌ፤
8.
መንገሻ ሓጎስ ተጋደየ ከትግራይ ምእራባዊ ዞን ፀለምቲ ወረዳ ሰፊዃ ቀበሌ።
9.
መኮነን አዱኛ ኪዴ ከትግራይ ምእራባዊ ዞን ፀለምቲ ወረዳ እንዳ መድሃኒ-አለም
ቀበሌ ዓዲ-ግርማይ ቀጠና፤
10. ትርሓስ
ድራር ብርሃነ ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራባዊ ዞን ታሕታይ አድያቦ ወረዳ አደመይቲ ቀበሌ ምልፃይ ቀጠና
11. በሪሁ
ወልዳይ ገብሩ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ወርዒ-ለኸ ወረዳ ወርዒ ቀበሌ ዕዲስመ-አስራትና ሌሎችም የሚገኙባቸው ወጣቶች ሁነው- እነዚህ
ወጣቶች ከትህዴን ጋር ተሰልፈው ለመታገል ያስገደዳቸው ዋነኛ ምክንያት ሲገልፁ።- በአሁኑ ጊዜ ሃገራችን ባለው ፀረ ህዝብ ስርዓትና
በተከሰተው ድህነት ምክንያት በርካታ ሴቶች የሚገኙባቸው ወጣቶች ሃገራቸውን
ትተው እግራቸው ወደ አመራቸው እየተሰደዱ መሆናቸውና ለራሳቸው ደግሞ ወደ ስደት ከመሄድ ይልቅ መሳርያ አንግተውና ወገባቸውን አጥብቀው
ይህን ለህዝብና ለሃገር መንቀርሳ የሆነውን ገዢውን የኢህአዴግ ስርአት ከስር መሰረቱ ለመገርሰስ ጊዜውና አማራጩ አሁን መሆኑን ተረድተው
ወደ ትህዴን ለመቀላቀል እንደወሰኑ ገልፀዋል።
በተለይ ደግሞ ወጣት አታሉ ተስፋ እንደገለጸው አንድን ዜጋ በአንድ ቦታ
ለስድስት ወር ያህል ከተቀመጠ መታወቂያ ካርድ እንደሚሰጠው የስርአቱ ህግ ቢያስቀምጥም ቅሉ እኛ ግን እድሪስ የተባለው ቦታ አንድ
አመት ያህል ተቀምጠን መታወቂያ ካርድ እንዳንወሰድ ተከልክለናል፤ በስብሰባ ወቅት ከነዋሪው ህዝብ ጋር እንዳንሰበሰብ ተከልክለናል፤
እንደ ጠላት እየታየን ተነጥለን ስንኖር ቆይተናል ሲል መግለፁን ሪፖርተራችን ከማሰልጠኛ ማእከል ጨምሮ አስርድቷል።