Saturday, May 23, 2015

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለምረቃ በተቃረቡበት ሰዓት የአብዛኛዎቹ ውጤት ዝቅተኛ መሆኑ ሲነገራቸው አመፅ ለማስነሳት እንደ ተደራጁ ተገለፀ።



     በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች የሚመረቁበት ሰዓት በተቃረበበት ጊዜ የነጥባቸው ውጤት ዝቅተኛ እንደሆነ ስለተነገራቸው ግንቦት 11/2007 ዓ.ም አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ግርግርና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ውስጥ ለውስጥ ከተደራጁ በኋላ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ዳግመኛ ግምት እንሰጠውአለን በማለት ምርጫው እስኪያልፍ የማታለያ መልስ እንደሰጣቸው ታወቀ።
   የኢህአዴግ ስርዓት የሃገራችንን ዩኒቨርሲቲዎች ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረጋቸው በመሆኑ የተነሳ ተማሪዎቹ እራሳቸውንና ሃገራቸውን ሊለውጥ የሚችል እውቀት ይዘው ከዩኒቨርሲቲ እንደማይወጡና ደህና ነጥብ አግኝተው የሚመረቁትም ቢሆን የኢህአዴግ አባላት ካልሆኑ ስራ ማግኘት እንደማይችሉ ይታወቃል።