በአማራ ክልል ደባርቅ ወረዳ የአምባ ጊዮርጊስና የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች
በአካባቢያቸው ለምርጫ የሚወዳደር ተቃዋሚ ድርጅት ባለመኖሩ የምርጫ ካርድ አንወስድም ብለው መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው የገዥው
ስርዓት ካድሬዎች ግንቦት 11 /2007 ዓ/ም ህዝቡን በመሰብሰብ የምርጫ ካርድ ያልወሰደ ዘይት ይሁን ስኳር አንሰጥም ጥቅማትቅም
ማግኘት ከፈለጋችሁ ካርድ ጠፋብን እያላችሁ አውጡና ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.ን ምረጡ በማለት እያስፈራሯቸው መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን
መረጃ አመለከተ።
ህዝቡ በበኩሉም
ስኳርና ዘይት ለርካሽ የፖለቲካዊ ጥቅም ማግኛ ትጠቀሙበታላችሁ ህዝብ ግን በዚህ አይታለልም በማለት የካድሬዎችን ብልሹ አሰራር እንደተቃወሙት
ሊታወቅ ተችሏል።