በምንጮቻችን
መረጃው መሰረት በደቡብ ህዝቦች ክልል ከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሚገኝ ህዝብ በኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ምክንያት ተቸግሮ እንዳለ
ከገለጸ በኋላ በዱራሜ ከተማ በተለይም ከሰኔ 25 /2007ዓ/ም ጀምሮ የመብራት ሃይል አገልግሎት ስለሌለ ነዋሪውን ህዝብ እለታዊ
ኑሮውን ለማሳለጥ እንዳልቻለና በተለይ ደግሞ የሆቴልና ቁርስ ቤት ባለቤቶች የሆኑት ነጋዴዎች ከአስተደደሩ መፍትሄ በማጣታቸው የተነሳ
ድርጅታቸውን ለመዝጋት እንደተገደዱ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው አስተዳደሩ ጥያቄውን ላቀረቡት የከተማው ነዋሪዎች
መልስ ሲመልስ ማንነታቸው ባልታወቁት ሰዎች የመብራት መስመሩን እንደተበለሸና ለተወሰነ ጊዜ ታጋሱን በማለት ያለ አንዳች ለውጥ ለአንድ
ወር ያህል ሳይስተካከል እንደቀረነና በዚህ ኢ-ፍታዊ ተግባር ተስፋ ያጡት ነዋሪዎችም ለሃምሌ 8/ 2007ዓ/ም ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ
በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።