Sunday, July 26, 2015

በመቐለ ከተማ የሚገኙ የዞንና የወረዳ ባለስልጣናት መቀሌ ውስጥ በፕላኔት ሆቴል ያካሄዱትን ስብሰባ ያለምንም ፍሬ መበተኑን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



    የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በዞንና ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎችና ባለስልጣናት በመቐለ ከተማ ፕላኔት በተባለው ሆቴል ተሰብስበው ኢኮኖሚያችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ማሸጋገር አለብን በማለት ሊቀሰቅሷቸው በሞኮሩበት ሰዓት ተሰብሳቢዎቹ በበኩላቸው እያላችሁት ያለ ገና ያልደረሰነውና መሬት ላይ ካለ ተጨባጭ ሁኔታ የማይጣጣም ነው በማለት መቃወማቸውን ተገልጿል።
   ተሰብሳቢዎቹ በማከል የእድገት መሰረት ልማት ከሆኑ እንደ መብራት፤ ውሃና የመሳሰሉትን አቅርቦት በሌለበት ከእርሻ  ኢንዱስትሪ ወደ ሚመራው ኢኮኖሚ እየተሸጋገርን ነን ማለቱ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ግምት ውስጥ የማያስገባ  ከሃቅ የራቀ ነው በማለት የቀረበውን አጀንዳ ስላልተቀበሉት ከስብሰባው ሳይረዳዱ መበተናቸውን የተገኘው መረጃው አክሎ አስረድቷል።