የአማራና የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ከዚህ በፊት በቆየ የመሬት አለመግባባት
በተነሳ ግጭት ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን እየሞቱ የሁለቱ ክልል የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ጉዳዩን በትኩረት አይተው እልባት ከመስጠት
ይልቅ በቸልተኝነት እያዩት መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በዚህ ምክንያትም
በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ግጨው በተባለ ቦታ ሃምሌ 13 ቀን 2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች አንድ
ዜጋ ተገድሎ መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ተገድሎ የተገኘው ወገን የትግራይ ክልል ተወላጅ ሲሆን ሁኔታውን ተከታትሎ
የሚያጣራ አካል እንደሌለ የገለፀው መረጃው ይህም ገዢው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ባለስልጣናት ሁለትም ብሄሮች በግጭት እንዲኖሩና አንድነት እንዳይፈጥሩ ለማድረግና የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም
የሚጠቀሙበት መላ መሆኑን ታውቋል።