በገዢው የኢህአዴግ ስርአት ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ አቅራቢነት።
ህዝባዊ ውክልና በሌለው “የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” አፅዳቂነት መስከረም 23 2008ዓ/ም ለ30 የካቢኔ ሚንስትር የተሰጠው
ሽመት ስራና ሞያ ያላገናዘበ፤ የአገርና ህዝብን ጥቅም ግምት ውስጥ ያላስገባ፤ በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ ቡዱን የፖለቲካ ጥቅም ብቻ ተብሎ የወንበር ቅይይር የታየበት አስመሳይና አስልቺ
እንደሆነ እነኚህ አገር ወዳድ የፖለቲካ ሙሁራን ለመገናኛ ቡዙኃን በሰጡት ሃሳብ አረድቷል።
አክለው እነዚህ የፖለቲካ ሙሁራን የካቢኔ ሚንስትሮች የአንዲት አገር
የደም ስር እንደመሆናቸው መጠን በሚንስትርነት የሚመሩት መስሪያ ቤት የሚመጥን በትምህርት የዳበረ ሞያና አቅም መኖራቸው በማረጋገጥ እንጂ ኢህአዴግ እንዳደረገው
መመዘኛው የፖለቲካዊ ታማኝነት አድርገህ ሽመት መስጠት የኢኮኖሚ እድገት ሊያመጣ ስለማይችል አገርና ህዝብ የማይጠቅም ኢ-ሃላፊነታዊ
አሰራር መሆኑን ሙሁራኑ በአንኩሮ አገንዝቧል።