Friday, December 25, 2015

በጋምቤላ ክልል የሚኖሩ የህብተረሰብ ክፍሎች በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት ቀጣይነት እየተንከራተቱ እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ገለፀ።



      የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብት ኮምሽን በአገር ደረጃ በታህሳስ 8/ 2008 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ ባከበረበት ጊዜ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የምክክር መድረክ እንዳደረገ ከገለፀ በኃላ በተለይ ደግሞ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች አንድ ጉዳይ ለማስፈፀም በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት ለወሮች ያህል እንዲንከራተቱ ምክንያት እንደሆነባቸው መግለፃቸው መረጃው ገልጿል።
    በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የፌደራል ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ደ/ር መንበረ ፀሃይ ታደሰ የተገኙ ሲሆን በተሳታፊዎች በኩል የቀረበው አቤቱታ በክልሉ ይሁን በከተማው የሚገኙ የፅህፈት ቤት አገልግሎት ሰጪ የመንገስት አካላት ጉቦ መቀበል እንዲሁም በዘመድ አዝማድ የሚሰራ አሰራር ምክንያት የሚደረሰው እንግልት። በአስተዳደሩ የሚወሰድ እርምጃ ካለ መኖሩ የተነሳ በውጤቱም ችግሩ የከፋ እንዲሆን እያደረገው እንዳለ የገለፁ እንኳ ቢሆንም ደ/ር መንበረ ፅሃይ ግን “መልካም አሰተዳደር ያለመኖሩ  የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈፀመ ነው የሚቆጠረው” ከሚል ባለፈ ለተሳታፊው የሚያረካ መላሽ ሳይሰጥ ኣንደተቆጠበ ለማወቅ ተችሏል።