Friday, December 25, 2015

በጭልጋ ወረዳ በአማራና ቅማንት ብሔረሰቦች መካከል የተነሳ ግጭት መቛጫ ባለመደረጉ የቅማንት ተወላጆች ለድህንነታቸው ሲሉ መጠለያ እየፈለጉ መሆናቸውን ተገለፀ።



    የአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ነዋሪዎች የሆኑ የቅማንትና ኣማራ ብሔረስቦች ባለፈው ጊዜ በኢህአዴግ መሪዎች ተንኮል የተነሳ ግጭት። በአሁኑ ጊዜም ተጠናክሮ እየቀጠለ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው፣ በዚህ መፍትሄ ያላገኘ ግጭት ለህይወታቸው ዋስትና ያጡ የብሔረሰብ ቅማንት ተወላጆችና በአካባቢው ሲኖሩ የቆዩት የትግራይ ተወላጆች ሌላ አማራጭ አጥተው ወደ መከላከያ ሰራዊት ካምፕ እየሄዱ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
     በዚህ መሰረት ደግሞ የቅማንት ብሔረሰብ በአማራ ብሔረሰብ እየታደናችሁ ነው የሚል የማስፈራርያ ቃል እየተነገራቸው ስለሚገኝ፣ በዚህ ሰግተው ሳይወዱ በግድ በአካባበው ወደ ሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች እንዲጠጉ በተገደዱበት ጊዜ ዉስጥ በወታዶሮቹ በጥርጣሬ አይን እየታዩ የተለያየ ችግሮች እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የብሔረሰቡ ተወላጆች ያስረዳሉ።