Thursday, January 28, 2016

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፣ የማህል ዳኛ ሆኖ ሲሰራ የነበረው የውሃንስ ገብረመድህን የተባለ ግለ ሰዉ በሙስና ተጠርጥሮ ለመጣራት ታስሮ በነበረበት ግዜ፣ ለፖሊስ ግቦ በመስጠት እንዳመለጠ ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት፣ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በፍርድ ቤት ማህል ዳኛ ሆኖ ሲሰራ የቆየውን የዉሃንስ ገብረመድህን የተባለ ሹመኛ፣ በሙሱና ተጠርጥሮ በሕግ ስር እንዲዉል  ከተደረገ በኃላ፣ የፖሊስ አባላት አጅብው ወደ ፍርድ ቤት እየወሰዱት በነበሩትበት ግዜ፣ ለፖሊሰቹ 40 ሺ ብር ግቦ ከሰጣቸው በኃላ ሮጦ እንዳመለጠባቸው አስመስለው እንዲጠፋ እንዳደረጉት ለማወቅ ተችሏል።
   የዉሃንስ ገብረመድህን ቀደም ሲልም የፍትሕ አካል ሆኖ እየሰራበት በነበረ ግዜ፣ በሙሱና ምክንያት ታስሮ እንደነበረ የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድተዋል።
    በመጨረሻም፣ ይህ ተግባር በአሁኑ ግዜ በተለያዩ የስርአቱ ስራዎች ተሰማርተው በህዝብ ላይ እየፈፀሙት የቆዩ የብልሹ አሰራር ተግባር ከክፍተኛ የስርአቱ መሪዎች እስከ የፀጥታ አካላት የተያያዘ በመሆኑ፣ በሕግ ስር ገብተው እንዲጣሩ ከተደረገ ከብዙ ሰዎች ጋር ተያያዥ ስለሚያደርግ ሆን ተብሎ ነው በከፍተኛ እመራሮች ሚስጥራዊ መምርያ እንዲጠፋ የተደረገው  ሲሉ የተለያዩ የፖለቲካ ሙሁራን ይገልፃሉ።

No comments:

Post a Comment