Thursday, January 28, 2016

በቃፋታ ሑመራ ወረዳ የፍትሕ አካላት ተብለው የተቀመጡ ሰዎች በብልሹ አሰራር ዉስጥ በመዘፈቃቸው ምክንያት፣ የሚገባ አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም እየተባሉ በነዋሪው ህዝብ ዘነድ እንደተገመገሙ ምንጮቻችን ገለፁ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት፣ በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ በሚገኙ የፍትህ ፅፈት ቤቶች ሰራተኞች ስልጣናቸው ተጠቅመው የሚሰሩ የገዢው የኢህአዴግ ስርአት ሽሞኞች የስራ ሃላፍነታቸው ተገን በማድረግ፣ ጎቦ ለሰጠ አገልግሎት ሲሰጡት ግቦ ላልሰጣቸው ተገልጋይ ደግሞ የሚገባውን አገልግሎት በመከልከል የቆጠሮ ቀኖች እያራዘሙ ፍትሕ በማዛባት ስራ ተጠምደው ስለቆዩ ህዝብ በዚህ ሳምንት ጠንካራ ግምገማ እንዳቀረበላቸው ለማወቅ ተችለዋል።
   በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ የወረዳዋ አቃቤ ሕግ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የቆየ ኢፍረም ሃይለ የተባለ ግለ ሰው፣  በየቀኑ የሚሰራቸው ስራዎች ከግቦ ጋር የተሳሰረ ካልሆነ በስተቀር፣ ሕግ መሰረት ያደረገ ሕጋዉነት ያሟላ ስራ እንዳማይሰራና በዚህ መንገድም ለህዝባችን አታልሎ የማይገባውን ሃብት በመካበቱ የተነሳ፣ ሕግ በመዛባት ተጠምዶ የቖየ ሰው በመሆኑ በህግ ስር ዉሎ እንዲጠየቅ ህዝብ አስተያየት ስላቀረበ የመድረኩ መሪዎች እንዲመልሱ በእስር ቤት እንዲገባ ቢያድርጉትም፣ ነዋሪ ህዝብ ግን ሽሞኛውን የፈፀመው ጥፋት ተጣርቶ የሚገባው ቅጣት ያገኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ከመረጃው ለማወቅ ተችለዋል።

No comments:

Post a Comment