በደረሰም
መረጃ መሰረት፣ በትግራይ ክልል አሕፈሮም ወረዳ ሆያ ቀበለ በአሁኑ ጊዜ በድርቅ ተጠቅተው ለአንድ ቀን እንኳን የሚሆን ምግብ አጥተው
በከፍተኛ ችግር ወድቀው ያሉት ወገኖች በርከት ያሉት እንዳሉ ከገለፀ በኋላ፣ በድርቁ ምክንያት ለከፋ ርሃብና ችግር ለተጋለጡት ወገኖች
እንዲውል ተብሎ ከለጋሽ ድርጅቶችና አገሮች የተገኘውን፣ እንደ ስንዴ፤ ዘይትና ምስር በገዢው ስርአት ካድሬዎችና አስተዳደሮች በአግባቡ
ከማከፋፈል ፈንታ፣ ሌላ ዘዴዎች በመፍጠር ለግል ጥቅማቸውና ለቤተሰቦቻቸው ጥቅም እያዋሉት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ፣ በህዝብ ስም ለተቸገሩ ወገኖች ተብሎ የተገኘውን እርዳታ
አስተዳዳሪዎቹ ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን እያጠፋፉት እንዳሉና ህዝቡም በበኩሉ፣ ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ የሚፈፅሙት ብልሹ
አሰራርና ስህተት ተግባር እንዲታረሙለት በተለያዩ መድርኮች የሚነቅፍ እንኳ ቢሆንም፣ ተመልሰው እንደ ወነኛ ጠላት በመቁጠር ከተለያዩ
የመንግስት ጥቅማ ጥቅም ውጭ በማድረግ ኢኮኖሚያዊና ሞራላዊ ውድቀት እንደሚያወርዱለት በዚህም የተነሳ ህዝቡ አንገቱን እንዲደፋ እያረጉት
እንዳሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment