Friday, January 22, 2016

በአሕፈሮም ወረዳ ገርሁ ሰርናይ ከተማ ፍትህ ባጣ የመጠጥ ውሃ ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታ እየተጋለጡ እንደሚገኙ ተገለፀ።



በደረሰን መረጃ መሰረት፣ በማእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ገርሁ ሰርናይ ከተማ ስር የሰደድው የመጠጥ ውሃ ችግር እንዳለ ከገለፀ በኋላ፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ደግሞ ችግሩን በማየት ዘላቂ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ፣ ግዝያዊ ጥገና በማድረግ የአገርና የህዝብን ሃብት ለውጥ በማያመጣ ተግባር ጊዚያቸውን በማባከን ይህን ያክል ባጀት በስራ ላይ አውለናል በማለት በሚዲያዎቻቸው ለማደናገሪያ እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ተገለፀ።
    መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው፣ በገርሁ ሰርናይ ባለው የመጠጥ ውሃ ችግር ምክንያት ነዋሪው ህዝብ ጥራቱን ያልጠበቀ ከኩሬ ለሚመጣ አንድ ጀሪካን ውሃ ከ10 ብር በላይ እንዲገዛ ግድ ሆኖበት ስላለ፣ በዚህም የተነሳ ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ የከተማው ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ ህፃናት ለተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች እየተጠቁ ባሉበት ጊዜ የተማላ ህክምና ስለማያገኙ ለተደራራቢ በሽታዎች እየተጋለጡ እንደሚኙ ለማወቅ ተችሏል።

      በተመሳሳይ በኩል፣ በቃፍታ ሁመራ ማይ ካድራ ከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ጊዜ፣ መንግስት ችግሩን አይቶ መሰረታዊ መፍትሄ ባለማድረጉ የተነሳ፣ የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ከአንገረብ ወንዝ እየቀዳ ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ እየተጠቀመ በተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች እየተሰቃየ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
                    

No comments:

Post a Comment