ነፃነት
ፕሬስ ባረጋገጡትና የሚቀበሉ የአለማችን አገሮች በመገናኛ ብዙኃን ይፋ የሆነ ምክር ቤት በማቆም ከነፃነት ፕሬስ ጋር ተሳስሮ የዜጎች
ዴሞክራስያዊና ሰብአዊ መብት ሲጣስ ቅሬታዎችን በመሰብሰብ ጉዳዩ በሕግ ታይቶ ዉሳኔ በማግኘት በሰላም መረጋገጥ፣ ዴሞክራሲ በማስፈን፣
መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ ህዝብ በቂ የሆነ መረጃ ለማግኘት፣
ወቅታዊና ትክክለኛ ያልተዛባ ፍፃሜዎች ወደ ህዝብ በማድረስ ሚድያ የማይናቅ ተራ እንደሚጫወት ለሁሉም ግልፅ ነው።
ህዝብ በአገሩ ጉዳይ ለሚፈፀሙ በየቀኑ የሚከሰቱ ፍፃሜዎች መረጃ የማግኘት
መብት አለው ብቻ ሳይሆን፣ ከህዝባዊ ጥቅምና ሃላፊነት ርቀው በግላዊ ጥቅም ያተኮሩ ከታች እስከ ላይ ለሚገኙ መሪዎች ሲገኙም ካለ
መሸፋፈን እንዲጋለጡ ያደርጋል።
ለአንድ ዴሞክራስያዊ ስርአት ጠቓሚ የሆነ መረጃ፣ ሃሳቦችና አመለካከቶች
በነፃ እንዲሸራሸሩ በሚችሉበት መንገድ ለመረጋገጥ ፕሬስ እንደ ተቋማት የሆነ አይነት ገደብ እና ጫና ሳይደረግበት ነፃነቱ ጠብቆ
የተለያዩ ሃሳቦች እና አስተያየቶች ተቀብሎ የመስተናገድ ባህሪ ቢኖሮዉም፣
እንደ ኢትዮጵያ የመሰሉ ፍፁም አምባገነን የሆነ ቡድን ስልጣን ተቆጣጥሮ የህዝብ ዴሞክራስያዊና ሰብአዊ መብቶች ረግጦ
በሚመራበት ግዜ፣ የፕሬስ ነፃነት አረጋግጦ እዉነተኛ ዕለታዊ የአገር
ፍፃሜዎች ወደ ህዝብ ያደርሳል ብለህ መጠበቅ ዉጤቱ ባዶ ከመሆን አልፎ ፋይዳ የለዉም።
በዚህ መሰረት በስልጣን ላይ የሚገኝ የኢህአዴግ እምባገነን ስርአት ሲታይ
የይስሙላ ህጎች በማዉጣት የማይቀደም እንኳ ቢሆን፣ ለወጣው እና ለፀደቀው ህግ ተግባራዊ በማድረግ ግን ራሱ ገዢው ስርአት በአንደኛነት
እየጣሰ ከመጣ ቡዙ አመታትን አስቆጥረዋል።
በዚህ ቅርብ ግዜ የገዢው ስርአት ጠቅላይ ሚንስተር መንግስታዊ የሆኑ የሚድያ
ተቋማት አስፈላጊ የሆነ መረጃ ለመስጠት ስምምነት እንደተደረገ መገናኛ ብዙኋን ደግሞ በበኩላቸው የሚገባቸው መረጃ ለህዝብ በጊዜው
ለማድረስ ከመንግስት አካላት መረጃ ለማግኘት የመንግስት ፍላጎት ሙሉ ነው ብሎ ነበር።
ቢሆንም ግን በሚሉት ደረጃ፣ መረጃ ወደ ህዝብ ሊደርስ ይቅርና እነሱ እምነው
በሰጡት ፋቃድ ተከትሎ መረጃ ያስተላለፈ፤ የፃፈና ሂስ ያቀረበ ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ ሞያዊ ሃላፍነቱ በመስራቱ ብቻ በወንጀል እየተጠየቀና
ከስራው እየተባረረ ባለበት በአሁኑ ጊዜ፣ ከዚህ አልፎም በስርአቱ ስር ባልዋለው ወንጀል ለአመታት እስራት በመፍረድ ባጠቃላይ የፕሬስ
ነፃነት ከአገራችን ኢትዮጵያ ጠፍቶ ባለበት ግዜ ነው። በአንድ በኩል የመገናኛ ቡዙኋን ኢንዱስትሪ መመስረት አገሪቱ በምትፍልገው
መንገድ እድገትና ብልፅግና ለመቀጠል ተበታትኖ የቆየ የመገናኛ ቡዙኋን ተቋማት በአንድ አይነት መተዳደርያ ደንብ ያለው ምክር ቤት
የተመሰረተ ሲሉ፣ በሌላው እዉነተኛ መልኩ ሲታይ ደግሞ ሁሉም የሚድያ አካላትና ተቋማት፣ ያልተስማሙበት የስርአቱ ጥቂት የቐኝ እጅ
የሆኑ ግለሰዎች የወሰኑት መሆኑ የሚታወቅ ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ በፀረ ሽብር ሽፋን አዋጅ ምክንያት ታጥሮ በምገኝበት ጊዜ፣ ንፁሃን
ፀሓፊዎች በእስር ቤት በሚገኙበት፣ ዜጎች አማራጭ ሚድያ እንዳያገኙ በታፈኑበት፣ አንድ ጋዜጠኛ ሞያዊ ስራዉን በነፃነት በማይሰራበት
አሁን ምክር ቤት መመስረቱ ለምን አስፈለገ፣ ሁሉም ዜጋ ሊጠይቃቸው ይገባል። ሰለሆነም በአንድ አገር የፕሬስ ነፃነት በሌለበት ጊዜ
ምክር ቤት መመስረቱ ለምን ምክንያት ይሆን?
No comments:
Post a Comment