Wednesday, February 3, 2016

በሃዋሳ ከተማ ዩንቨርስቲ ውስጥ የሚገኝ የፈሳሽ ቆሻሻ መጠራቀምያ መከላከያ ስላልተሰራለት 3ት ህጻናት ወደ ዉስጥ ገብተው መሞታቸው ተገለጸ።



እነዚህ የሞቱ ህጻናት የ12፤ የ8ና የ14 አመት ዕድሜ ሲሆኑ ለመሞታቸው ምክንያት የሆነ ደግሞ ከዩንቨርስቲው የሚወጣ ቆሻሻ  መጠራቀምያ ወይም ዋስትና ያለው አጥር በመንግስት ባለ መሰራቱ ህጻናቱ ለመጫወት ብለው ከመኖርያ ቤታቸው ከወጡ በኃላ፣ በቆሻሻ መጠራቀምያ ጉድጋድ ገብተው መሞታቸው ለማወቅ ተችሏል።
     በቀብር ስነ ስርአቱ የተገኙ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎች፤ የከተማዋ አስተዳደር ለዜጎች ደህንነት በተለይ ደግሞ ለህጻናት ግምት ዉስጥ ያላስገባ የቆሻሻ መጠራቀምያ ጉድጋድ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ መስራት ባለመቻሉ ምክንያት ህጻናት ልጆቻችን እና ወንድሞቻችን እንደዚህ በመሰለ አሰቃቂ ሁኔታ ሊሞቱ መቻላቸው ይህ ደህሞ የ3ቱ ህጻናት ልጆች ሞት ምክንያት መንግስት ሃላፍነት መወስድ አለበት ሲሉ ብሶታቸውን   እንደገለጹ መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል።

No comments:

Post a Comment