Wednesday, February 3, 2016

በውጭ የምንዛሬ እጥረት ለእርሻ የሚያሰፈልግ ማደበሪያ በውቅቱ ለማቅረብ ባለመቻሉ በመስኖ ሰራ የተሰማሩ ገበሬዎች ለችግር እየተጋለጡ መሆናቸው ተገለጸ።



በዚህ ወቅት በአገራችን ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት በስፊው አጋጥሞ ስለሚገኝ  ከውጭ ተገዝተው የገቡ አስፈላጊ ነገሮች መግዥያ የሆነ ዶላር በመንግስት ሊቀርብ ባለመቻሉ የተነሳ በማሕበራዊና ኢኮነምያዊ ዘርፍ ከባድ ችግር አሳድሮ እንደሚገኝ ከገለጹ በሃላ። በተለይ ደግሞ በእርሻ ስራ አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ መዳበርያ የኢህአዴግ ገዢ ስርአት በህዝብ ጥያቄ መሰረት ወደ ገበሬዎች ለማቅረብ ባለመቻሉ በመስኖ ስራ ላይ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል።
       መረጃው ጨምሮ እንደሚያስረዳው፣  በወጣዉ ሪፖርት መሰረት በአሁኑ ጊዜ ለገበሪዎች ተሰጥቶ ለመስኖ ስራ እንዲዉል የሚገባው መዳበርያ 833.663 ሜትሪክ ቶን ሊሆን ሲገባው፣ በዉጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት እስከ አሁን ድረስ ቀርቦ ያለው መዳበርያ 19.315 ሜትሪክ ቶን ብቻ አገር ዉስጥ የገባ ሲሆን ለዚህ የውጭ ምንዛሬ መጥፋት ምክንያት ደግሞ ከዉስጥ አገር የሚላክ ምርት በጣም በመጉደሉ የተነሳ መሆኑ መረጃው አገንዝበዋል። 

No comments:

Post a Comment