Friday, February 5, 2016

በፖለቲካና በኑሮ ችግር ምክንያት አገራቸውን ጥለው ታንዛንያን አቋርጠው የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ እንግልትና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን ተገለፀ።



        በመረጃው መሰረት፣ በምስራቅ አፍሪካ ወደ ምትገኘው  የታንዛንያ ግዛት  ወደ  ሆነችው በመግባትና ከዚያም  ወደ ደቡብ አፍርካ ለመጓዝ የሞኮሩ ኢትዮጵያውያን  ሰደተኞች፣  በቁጥጥር ስር የዋሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን መንግስት ሃላፍነት ወስዶ  ሊረከባቸው ባለመቻሉ ምክንያት  የታንዛንያ መንግስት በበኩሉ በሃይል  ወደ አገራቸው    እንደሚመልሳቸው የታንዛንያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር  ቻርለስ ኪታዋንጋን ጥር 17 ቀን 2008 ዓ/ም  ለሮይተር  የዜና አውታር በሰጡት መግለጫ አሳውቋል።
         መረጃው ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ  የደረሰው  መጠነ ሰፊ   የሆነ  ረሃብ  ምክንያት ተማርረው አገራቸውን ጥለውና ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ብለው  ለደላሎች ከአንድ ሺ  እስከ ሁለት ሺ  ዶላር  በመክፈል  በታንዛንያና በማላዊ አቋርጠው   ደቡብ አፍሪካና ኤውሮፓ ለመሄድ በማሰብ  ሲጓዙ የነበሩት ዜጎቻችን   በአገሪቱ የፀጥታ ሃይሎች ተይዘው በቁጥጥር ስር ላይ የወደቁ ኢትዮጵያውያን  በገንዘብና በእስር በመቅጣት  በማንገላታት  ወደ አገራቸው    እያባረርዋቸው   መሆናቸውን  መረጃው  ጨምሮ አስረድቷል።
               


No comments:

Post a Comment