በተለያዩ ምክንያቶች በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች በእስር ቤቱ ሃላፊዎች
መንገላታት እየደረሰባቸው መሁኑንና ጥር 20/ 2008
ዓ/ም ደግሞ
በእስር ቤቱ በተነሳው ግርግር ምክንያት በተያያዘ “የእስር ቤቱ ሃላፊ እናንተ ናቹሁ ይህንን ግጭት እንዲነሳ ያደረጋችሁት” በሚል ምክንያት
አስጊዎች ናቸው ያላቸው ወገኖች ባልዋሉበት ተግባር በላያቸው ላይ
ግፍ እያወረደባቸው መሆኑን መረጃው አስረድተዋል።
መረጃው
ጨምሮ እንዳስረዳው፣ በቃሊቲ እስር ቤት በተነሳው ግጭትና ግርግር
የታሰሩት አብዛኛዎቹ ከደሴ ተከሳሾች በተያያዘ
ለምስክርነት ተጠርተው በችሎት ላይ መሆናቸውን እየታወቀ። ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የእስር ቤቱ ሃላፊ
በእስሮኞቹ ላይ ሃይል በመጠቀም ግፍ እንዳወረደባቸው ታውቋል።
በመጨረሻ
ዘገባው፣ በቃሊቲ እስር ቤት ታስረው የሚገኙ ወገኖች ባለፉት አመታት የተለያዩ እንግልት እየደረሰባቸው እንደቆየና። ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙም በማገድ ብርሃን በማይገባበት ጨለማ ቤት በማሰርና ሞራላቸውን
በመስበር የተለያየ የግፍ አይነቶች በመጠቀም በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ በባሰ ሁኔታ
እየሰሩበት መሆናቸውን መረጃው ገልፀዋል።
No comments:
Post a Comment