Wednesday, February 10, 2016

በጋምቤላ ክልል የተነሳውን የጎሳ ግጭት መፍትሄ ለማምጣት የሚሰራ የመንግስት አካል ባለመኖሩ የተነሳ፣ እስከ አሁን ድረስ ግጭቱ በመቀጠል ላይ በመሆኑ ቡዙ ዜጎች የሞትና የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ተገለፀ።



       ከሳምንት በፊት በጋምቤላ ክልል በአኝዋክ ብሄርና ኑዌር መካከል የተነሳውን ግጭት ገዢው የኢህአዴግ ስርአት ግጭቱን ለመግታት  ሃላፊነት  ወስዶ ሊሰራ ባለመቻሉ፣ ግጭቱ አሁንም ተባብሶ እየቀጠለ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው፣ በዚህም ምክንያት ቡዙ ንፁኃን ዜጎች ህይወታቸው እያለፈና ቤት ንብረታቸውን በመቃጠል ላይ በመሆኑ የተነሳ፣ የክልሉ ተወላጅ የሆኑት ወገኖች ቤታቸውንና ንብረታቸው በመተው ወደ ተለያዩ ጎሮቤት አገሮችና ክልሎች እየተሰደዱ እንዳሉና፣ በገዢው ስርአት ላይም ተቃውሟቸው በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
        መረጃው በመጨመር፣ በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ተወላጆች የሆኑትን ዜጎች በተነሳው ግጭት ቀንደኛ ተጠቂዎች እንደሆኑና፣ ለደህንነታቸው ዋስ የሚሆናቸው የመንግስት አካል ሊያገኙ ባለመቻላቸው ምክንያት፣ ቤት ንብረታቸው ጥለው በመሸሽ ከአካባቢው እየራቁ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment