Tuesday, February 16, 2016

የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪዎች የወልቃይት ፀገዴ ነዋሪዎች ያነሱት ጥያቄዎች ስለ አስጨነቃቸው ህዝብን በማሰር ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ተገለፀ።



ህዝብ አነሳስታቹሃል ተብለው ከታሰሩት  የወልቃይት ነዋሪዎች ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ።  ሹሙዬ ገብሩ የተባለ ኢንቨስተር፤ ነጋ ባንቲና አቶ ሃይለማርያም የተባሉ እንደሚገኙባቸውና በተለይ ሃዱሽ አለሙ የተባለ የሁመራ ከተማ ቀበሌ ሶስት አስተዳዳሪ የሆነው ። ከእያንዳንዱ ኢንቨስተር 2ሺህ  ብር በድምሩ  ግማሽ ሚልዮን ብር ተቀብለሃል። ህዝብ  አነሳስተሃል በሚል ጥር 30 .2008 ዓ/ም  እንደታሰረ  ያገኘነው መረጃ አስረድተዋል።
    በሁመራ  ከተማ  በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ  ስብስባ   ካሕሳይ  ኣበራ የተባለ ሆስፒታል  ተገቢውን ህዝባዊ አገልግሎት ኣይሰጥም፤ መድሃኒት የሚባል ነገር የለውም፤  መንግስት የምያቀርበውን መድሃኒት ወዴት እየጋባ ነው?  ከተመረመርክ  በኃላ መድሃኒት ከፋርማሲ ግዛ ትባላለህ፤  መንግስት ቁጥጥር አያደርግም፤ ዶክተሮች ወደ ሙስና ገብተዋል ፤ የሚሉትና ሌሎችም  ነጥቦች የቀረቡ ሲሆን ስብሰባውን የመሩት ደግሞ የከተማ ሑመራ ከንቲባ አቶ አለሙ አየነወና፤ የቀበሌ 03 የፖለቲካ  ሃላፊ ዓብደል ዋስዕ ሲሆኑ  ለቀረበላቸው ጥያቄም የሚገባ መልስ ከመስጠት ይልቅ ስበሰባውን  ያላአግባብ በሃይል ሲመሩት እንደሰነበቱ ታውቋል።
   በሌላ በኩል ደግሞ ባለፈው በህግ ቁጥጥር ውለው ይጠየቁ የተባሉ የመልካም አስተዳደር ጠንቅ ሁነው ከቆዩት 117 የገዥው ስርአት  ሹመኞች  አንዳንዶቹ ወደአልታወቀ  ቦታ እንደጠፉና፣ ከጠፉትን  የተወሰኑትን ለመጥቀስ ይባልህ የተባለ የትግራይ ምእራብ ዞን የፍትህ ቢሮ ሃላፊ የነበረና አቶ  ካልአዩ የከተማ ሁመር አቃቤ ህግ የነበረ  የሚገኙባቸው ሲሁኑ የነዚህ ሹመኞቹ  መሰወር የኢህአዴግ  ካድሬዎች እጅ እንዳለበት ምንጮቻቻን በመጨረሻ ገለፀዋል።  


No comments:

Post a Comment