Tuesday, February 16, 2016

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የእስልምና አማኞች ወገኖቻችን በድንገት በአንዋር መስጊድ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ማካሄዳችው ተውቋል።



     የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አዲስ ኣበባ ከተማ  ውስጥ የሚገኙ  የሙስሊም አማኞች  የካቲት 5 /2008 ዓ/ም  በአንዋር መስጊድ በጀሞዓ ፀሎት በነበሩበት ግዜ በድንገት የተለያዩ መፈከሮችን በማንገብ   ፀረ አምባገነን   የኢህአዴግ ስርአት  ደማቅ የተቃውሞ  ሰለማዊ  ሰልፊ ማካሄዳቸው ለማወቅ ተችልዋል።
     በሰልፉ ላይ ያሰምዋቸው  ከነበሩት መፈክሮች አንዳንዶቹ  ለመጥቀስ የሃይማኖት ነፃነት ይከበር፤  በአገሪትዋ  ዜጎች ላይ የሚወርደውን ግፍ  ይቁም፤  እስከ አሁን ድረስ በእስር ቤት ታጉረው የሚገኙ የሃማኖት መሪዎች ይፈቱ፤ እሱረኞቹ እስካልተፈቱና መንግስት በሙስሊም ሕብረተሰብ የሚካሂደው የፖለቲካ ቅስቀሳ እስካላቆመ ድረስ  ተቃውሞው ቀጣይ ነው፤ ወዘተ የሚሉትን የተለያዩ ጥያቂዎችን ማሰማታቸው የተገኘው መረጃ  አስረድተዋል።
    በመጨረሻ መረጃው  በአሁኑ ግዜ አዲስ አበባ ከተማ  ውስጥ የሚገኙ  የሙስሊም አማኞች ያነሱት ድንገተኛ  ሰለማዊ ሰልፍ  ለተወሰኑ ግዜያቶች ያቋረጠ እንኳን ቢምስል፣  ችግሮችና ጫናዎች ሊቀረፉ ባለመቻላቸው ምክንያት  ተቃውሞው በሰፊው እንደሚቀጥል የተለያዩ አካላት በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። 

No comments:

Post a Comment