Tuesday, May 2, 2017

የሰዎች ነፃነት በተገፈፈበት አገር ልማት ማምጣት ከቶም አይችልም፣፣



በአንድ አገር ነፃነት ለሰው ልጅ የተሰጠ ተፈጥሯዊ ፀጋ መሆኑ አይካድም ሰለሆነም በነፃነት ማሰብ፣ መናገርና መፃፍ የሰው ተፈጥሯዊ ባህሪ፥ የሰውነት የሰብዓዊነት መገለጫ ነው። በመሆኑም፣ ነፃነት የሌለው ሰው ሰብዓዊ ክብሩን የተገፈፈ ነው ሰዎችን በነፃነት ከመኖር፥ ከማሰብ፥ ከመናገር፥ ከመፃፍ፥ የሚያግዱ በሙሉ የሰው ልጅን ተፈጥሯዊ ባህሪ ለመግፈፍ የሚጥሩ ናቸው የሰው ልጅ የተፈጠረው ከምንም ዓይነት እዳና እገዳ ነፃ ሆኖ ሕይወትን በነፃነት እንዲኖር ለማድግ ቢደነገጉም በኢህአዴግ መንግሰት ግን  ሊረጋገጥ አልተቻለም ፣፣
የሁሉም ሰዎች ነፃነት የሚከበረው የእያንዳንዱ ሰው ነፃነት ሲከበር ብቻ  ነው እያንዳንዱ ሰው ግዴታውን በራሱ ከተወጣ የሁሉም ሰዎች ነፃነት ይከበራል ነገር ግን አንድ ሰው ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ መንግሰት ትልቅ ሚና መጫወት ይጠበቅበታል ስለዚህ ሕይወትን በነፃነት ለመምራት ሁሉንም ሰዎች የሚያምኑት እና ሁሉን ሰዎች እኩል የሚያደርግ መንግሰት ህዝቦች ቢመኙም በተግባር የሚሰራ ሊያገኙ  አልተቻሉም ፣፣
ሁሉም ሰው በራሱ ፍላጎትና ምርጫ ለመንቀሳቐስ በሚጥርበት ግዜ ነፃነቱ ከታገደ ከፍርሃት ነፃ ሊሆን አይችልም ።በዚህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ እርስ-በእርስ መተማመን ሊኖርና ልማት ሊመጣ ከቶም አይታሰብም።ይህ ያለመተማመን መንፈስ ደግሞ እርስ-በእርስ መፈራራትን  ሁሌም ለለውጥ ስጋት የተሞላ ጉዞ ነው ።
ምንግዜም ቢሆን ነፃነቱን የተነፈገ ህዝብ  ነፃነቱን እንድያገኝ ባገኘው አጋጣሚ ትግሉን ይቀጥላል ስለዚህ ሁሉም ሰዉ በራሱ ፍላጎትና ምርጫ በሚንቀሳቀስበት የነፃነት ሕይወት ውስጥ እያንዳንዱ ሰው የሌሎችን እንቅስቃሴ በእርግጠኝነት መገመትና ማወቅ ካልቻለ ተማምኖ ለመሰራት ያዳግታል በዚህ መሰረት በተወሰነ አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ማህበራዊ ግንኙነታቸውን የሚመሩበት የራሳቸው የሆነ ሕግና ሥርዓት ሊኖራቸው የግድ ይላል።
ትክክለኛ የሕግ ስርዓትን ለመዘርጋት ደግሞ ሦስት አካላት ያስፈልጋሉ እነሱም- ሕግ አውጪ፣ ሕግ ተርጓሚና ሕግ አስፈፃሚ እነዚህ ሦስት አካላት በጥምረት መንግስት ይባላሉ የእነዚህ አካላት ድርሻና ኃላፊነት በግልፅ ተለይቶ የሚቀመጥበት የውል ሰነድ ሕገ-መንግስት ተብሎ ይጠራል በዚህ መልኩ የተወሰነ ጂኦግራፊያዊ ክልል ያለውና በአንድ መንግስት አስተዳደር ስር የሚገኝ ግዛት ደግሞ ሀገር ይባላል።ሰለሆነም  በዚህ መልኩ፣ በአንድ የተወሰነ አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ነፃነትን ለማረጋገጥ እና ፍርሃትን ለማስወገድ ከእያንዳንዳቸው የበለጠ ኃይል ያለው መንግስት ነው ቢባልምን እንኳን ሊያሰከብርላቸው ቀርቶ ራሱ የግለሰቦችን ነፃነት በመግፈፍ ችግራቸውን በሰላማዊ ሰልፋ ለሚገልጡ ህብረተሰብ በአዋጅ በመደንገግ  በእስር ቤት በማጎርና በመግደል ላይ ተሰማርቷል፣፣
የመንግስት ስልጣን ማለት የዜጎችን ነፃነት እንዲያስከብር ከእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ ተቆርሶ የተሰጠ መብት ነው ምክንያቱም እያንዳንዱ ዜጋ አንደኛሌላውን መብት ሳይነካ የፈለገውን ነገር እየሰራ እየተናገረና እየፃፈ በሰላም በሀገሩ እንዲኖር፣ እና ሁለተኛ- በባዕድ ሀገር መንግስት ወይም በሌላ ሰው በኃይል ተገዢ እንዳይሆን ጥበቃና ከለላ እንዲያደርግለት ራሱን በራሱ የማስተዳደርና የመምራት መብቱን ለመንግስት በውክልና ቢያሰረክብም ሊጠበቅለት አልቻለም።
ስለዚህ መንግስት ለዜጎች ነፃነት ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንጂ ነፃነታቸውን ለመገደብ የሚያስችል ስልጣን አልተሰጠውም በመሰረቱ ፍርሃትን ለማስወገድ የተፈጠረ አካል ሌላ ፍርሃት መፍጠር የለበትም የሰው ልጅ ነፃነቱን ለማረጋገጥ ሲል ከነፃነቱ ላይ ቀንሶ የፈጠረው መንግስት ራሱ መልሶ ነፃነቱን ሊነፍገው አይገባም መንግስት የዜጎችን ነፃነት የሚነፍግ ከሆነ የተፈጠረበት ዓላማ ስቷል ብቻ ሳይሆን  የዜጎችን ነፃነት የሚነፍግ መንግስት በውጤቱ ደረጃ ሲመዘን  ፍይዳ-ቢስ ነው።
የመንግስት ሕልውና የተመሰረተው የዜጎችን መብትና ነፃነት በማክበርና በማስከበር ላይ ነው እየተባለ ቢደሰኮርም በተግባር ሲታይ ግን የዜጎች መብትና ነፃነት የሚረጋገጠው ደግሞ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባለመፈጠሩ እና ሶሰት የመንግሰት  አካላት የሚባሉት  ሥራና ኃላፊነታቸውን ነፃና ገለልተኛ በመሆነ  መልኩ መወጣት ሲችሉ ብቻ ነበር የኢህአዴግ መንግስት ሥራና ኃፊነታቸውን እንድዋጡ የተመቻቸ ቦታ ሊፈጥር ባለመቻሉ የዜጎችን መብትና ነፃነት ማክበርና ማስከበር አልተቻለም።
ፍርሃት በነገሰበት ሀገር በነፃነት ማሰብ ወንጀል ይሆናል በነፃነት መናገር ከአመፅ ይቆጠራል በነፃነት መፃፍ ለእስርና ስደት ይዳርጋል የሀገሪቱን ዜጎች በነፃነት ከመኖር፥ ከማሰብ፥ ከመናገርና ከመፃፍ የሚያግድ መንግስት ከእድገት ይልቅ ውድቀትን የመረጠ መሆኑን ለአገራችን ህዝብ የሚነገር አይመስለኝም ሰለዚህ የዜጎችን መብትና ነፃነት በተገፈፈበት አገር ልማት ማምጣት ከቶም አይችልም ፣፣

No comments:

Post a Comment