የኢህኣዴግ መንግሥት በኣዲስ ኣበባ 750 ሺሕ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ተይዘዋል እያለ ቢናገርም፣ በተግባር ግን የውጣ በጀት እንደሌለና ኣስደንጋጭ ሁኔታ እንደተፈጠረ ተገለፀ።
ይህ በ1996 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አዝጋሚ ጉዞ በማድረግ የተወሰኑ ቤቶች የሰራ ሲሆን፡ የዚያን ጊዜዎቹ ተመዝጋቢዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ማለት ከ13 ዓመታት አሰልቺ ጥበቃ በኋላ ፡ ተገንብተው የሚጠናቀቁ 30 ሺሕ ቤቶችን እንደሚከፋፈሉ ይጠበቃል፡፡
መንግሥት ፖሊሲ ከማውጣትና ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ በግሉ ዘርፍ ሥራ ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ሲማስን በመክረሙ፣ እጅግ አንገብጋቢ መሠረታዊ ፍላጎት የሚባለውን የቤት ችግር ሊፈታ አልቻለም፡፡ ይህ የሚያሳየው የፖሊሲ ውድቀት መሆኑንም ተገልጿል።
በ2005 ዓ.ም. አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ቤት ፈላጊ የከተማ ነዋሪዎችን በ10/90፣ በ20/80 እና በ40/60 መርሐ ግብሮች በመመዝገብና ንግድ ባንክ እንዲቆጥቡ በማድረግ ግንባታ ቢጀመርም፣ በተለይ በ40/60 አንድም ቤት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ አልተቻለም፡፡
የቤቶቹን ሙሉ ክፍያ ከፈጸሙ ጀምሮ በየወሩ ያለማቋረጥ የሚቆጥቡ ዜጎች ግዴታቸውን እየተወጡ ቢሆንም፣ መንግሥት ያለ ሥራው የገባበትን ፕሮጀክት ማስፈጸም ባለመቻሉ ብቻ ተስፋ ቆራጭነት ሰፍኗል፡፡
በመጨረሻ የአገሪቱ ዋነኛ መሠረታዊ ችግሮች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ የመኖሪያ ቤት እጥረት በመሆኑ ይህንን መሠረታዊ ችግር ማስታገስ የሚቻለው ደግሞ በጥናት ላይ የተመሠረተ አሠራር ተግባራዊ ሲደረግ ብቻ መሆኑም ተገልጿል።
No comments:
Post a Comment