Monday, August 7, 2017

በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ የሚኖሩ ወገኖች፣ በንፁ የመጠጥ ወሃ እጥረት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገለፁ።



በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ የሚገኙ የጮጮሆ ቀበሌ ነዋሪዎች፣ ንፁ የመጠጥ ዉሃ አጋጥምዋቸው እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
ወሃ ለማግኘት ሲሉ ረጅም ሰአታት እንደሚጓዙ የገለፁት ወገኖቹ፣ ረጅም ሰአታት ተጉዘህ የምታገኘው ወሃ የሚቀዳበት ቦታም እናቶች ሌትና ቀን በብርድና ፀሓይ እየተሰቃዩ ተራ በመያዝ አንድ ጀሪካ ብቻ እንደሚደርሳቸውም  አስታዉቀዋል።
በተጨማሪም የተገኘችዋ አንዲት ቸሪካ 8 ብር እየከፈሉ የሚወስዱት ሆነው፣ ወሃው ፅዳቱ የጠበቀ ባለመሆኑ፣ የአከባቢው ነዋሪ ህዝብ በተለያዩ ወሃ ወለድ በሽታዎች እየተሰቃየ እንደሚገኝ፣ ለማወቅ ተችለዋል።
በተመሳሳይ ዜጎቹ በአካባብያቸው ተከስቶ ያለው ረዥም ግዜ ያስቆጠረ የንፁህ ወሃ ችግር፣ መፍትሔ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሲጠይቁ የቆዩ ሲሆኑ፣ የክልሉ አስተዳዳሪዎች ግን በአጭር ጊዜ እንፈታላቹሃለን ከሚል የተለመደ የመደናገርያ ቃል አልፍው፣ እስካሁን ድረስ ያደረጉት አስተዋፅኦ እንደሌለ ወገኖቹ ጨምረው አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment