የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለፁት፣ ዩኒፎርም የለበሱም ያለበሱም የፖሊስ
አባላት የህብረተሰቡን እንቅስቃሴ እግር በእግር እየተከታተሉ እንደሚገኙ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ በቀበሌ የተመለመሉ ወሬ አቀባዮች
በየሰፈሩ መበተናቸውንም ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ፡፡
ከተማዋ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንድትገባ የሚደረገው፣ ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል የአገዛዙ ስጋት እንደሆነ ታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ሶስት ወይም አራት ሆኖ መቀመጥ አልያም ሻይ ቡና ማለት
እንኳን ክልክል እየሆነ መምጣቱን የገለጹት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ በየጫት
ቤቱ ሳይቀር ክትትል እንደሚደረግም ነዋሪዎቹ ተናግሯል፡፡ ከአስቸኳይ
ጊዜ አዋጁ በፊትም ቢሆን በአፈና ውስጥ የሚገኘው የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከአዋጁ በኋላ ደግሞ የባሰ የጭቆና ቀንበር ውስጥ
እንዲገባ መደረጉን እማኞቹ ያስረዳሉ፡፡
አገዛዙ የነዋሪዎችን ዕለታዊ እንቅስቃሴ በይበልጥ የሚቃኘው እና ወሬ
የሚሰበስበው በየቀበሌው በተሰገሰጉ ካድሬዎች አማካይነት ሲሆን፤ ሲቪል የለበሱ የፖሊስ አባላትም የስለላ ስራ እንደሚሰሩ
ይገልጻሉ። እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ መሸት ሲል ደግሞ በከተማዋ ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን፤ በከተማዋ ድንገተኛ
ፍተሻን ጨምሮ ሌሎች ድርጊቶች እንደሚከናወኑ የገለጹት እማኞች፤ የከተማዋ ነዋሪ በተለይ ከአዋጁ መጽደቅ በኋላ ድርብ አፈና
ውስጥ መግባቱንም የእማኞቹ ገለጻ ይጠቁማል፡፡
No comments:
Post a Comment