Sunday, August 30, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች በወታደሮችና በፌድራል ፖሊሶች ህገወጥ ፍተሻ ምክንያት እለታዊ ስራዎቻቸውን ለማከናወን መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።



ነዋሪዎች እንደተናገሩት ከነሃሴ 17 ቀን 2007 ዓ/ም በፍኖተሰላም ከተማ በተሰማሩት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት ጋጋታና ትርምስ እለታዊ ስራቸውን ለመስራት እንደተቸገሩ የገለፁ ሲሆን ወታደሮች እና የፌድራል ፖሊሶች በየቤቱ እየገቡ ምንም ዓይነት የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ በህገወጥ መንገድ ቤቶችን በነፍስ ወከፍ እየፈተሹ መሆኑን አብራርተዋል።
    የንፁሃን ዜጎች የመኖሪያ ቤት በህገወጥ መንገድ የሚፈተሽበትን ምክንያት አንዳንዶቹ ሲናገሩም ከኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አንድ ባለስልጣን ከሁለት ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ተቃዋሚዎችን ለመቀላቀል ከአዲስ አበባ  ወደ ፍኖተሰላም ገብቷል በሚል ግብረ ሽበራ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።